Daily Archives: February 24th, 2015

የኢትዮጵያ ማህበራዊ አገልግሎት (2015) አመታዊ የሴቶች ቀን ክብረ በዓል

ዓለም አቀፍ  የሴቶች ቀን የካቲት ፳፱ (March. 8)

በመላው ዓለም በየዓመቱ በየካቲት 29 ቀን ይንም (March 8.) የሲቶች ቀን በመባል  በታላቁ ይከበራል ። ይህንኑ በማጠናከር የኢትዮጵያ ማህበራዊ አገልግሎት በዓሉን  ምክንያት በማድረግ የውይይት መድረክ አዘጋጀቶአል። ለሴቶች መብትና ጢንነትን በተመለከተ በየጊዜው ብዙ ሽግግርና ማሻሻያም ተደርጓል ይሁንንና ችግሩ በተለየ መልኩ በመከሰት የሚፈለገው ደረጃ ላይ መድረስ  አልቻለም። ይሁንና የሴቶችን ችግር ገጠመኘን ለማሻሻል ና መፍተሄ ለማግኘት የውይይት ዝግጀት ተይዟል. አርስዎም የዚሁ ውይይት ተካፋይ እንዲሆኑ ተጋብዘዋል።

እንድሚታወቀው የኢትዮጵያ ሴትች በተለያየ መንገድ ኑሮን ለማሸነፍ ወደ ጎሬቤት የአረብ ሀገር በሕግም ሆነ ካለህግ ካሀገራቸው ውጪ በመሄድ የደረሰባቸው ችግር እጅግ አሳዛኝና አስደንጋጭ ነው ይህንን ሁኔታ ያላየ ያልሰማ የለም። ታዲያ መፍተሄው ምንድነው? አሁንም በሹሉክልክ ከሕግ ውጪ ወደዚሁ ሀገር ለሞትና ለባርነት በመሄድ ላይ ይገኛለኡ።

በውይይቱ ላይ ተግኝተው የበኩልዎን ሃሳብ ይስጡ በማለት የኢትዮጵያ ማህበራዊ አግልግሎት ኮሚቴ በአክብሮት ያሳስባል.!

%d bloggers like this: